የለውጥ መረጆዎች



”Strategy without tactics is the slowest route to victory. Tactics without strategy are the noise before defeat.”
(Commonly attributed to Sun Tzu)
contact us
ይህንን ገጽ የጎበኙ ሰዎች መጪውን አለም በራሳቸው እጅ ለመገንባት የሚያስችሉ የግንባታ መሳሪያዎችን በመታጠቅ ከተጠቂነት ወደ ለውጥ ተዋናይ እና መሪነት ይሸጋገራሉ የሚል ሙሉ እምነት አለኝ። ለማነኛውም ጥያቄ ወይም መልእክት በ hizbawiabiyot@gmail.com
ትኩስ ዜናዎች እና ትንተናዎች
Latest NEWS

የቴዲ አፍሮ አዲስ አልበም፡ የጥበብ ስኬትና የፖለቲካው ትኩሳት
አዲሱና ‘ኢቶሪካ’ የተሰኘው የቴዲ አፍሮ አልበም ከመውጣቱ በፊት፣ የአርቲስቱን የቆየ ታሪክና የስራዎቹን ተፅዕኖ ፈጣሪነት የተረዳው አገዛዝ፤ አልበሙ በታቀደለት መልክ ለህዝብ እንዳይደርስ እገዳ ሲጥል ቆይቷል። ይሁን እንጂ አርቲስቱ ስራዎቹን በግል የዩቲዩብ (YouTube) ገጹ ላይ በመልቀቅ፣ በሙዚቃ በአለም ገበያው ውስጥ ከፍተኛ የዕይታ ቁጥርና ስኬት ማስመዝገብ ችሏል። በተለይም በግጥሞቹ ውስጥ የሚንፀባረቁት ጥልቅ ፖለቲካዊ መልዕክቶችና ማህበራዊ ትችቶች የብዙዎችን ልብ ገዝተዋል። በአንጻሩ የአርቲስቱ ስራዎች ስልጣን ላይ ያለውን አካል የመሞገት ባህሪ ስላላቸው፣ የአገዛዙ ግብረ-መልስ በአፈና የተሞላ ነበር። በመንግስት ቁጥጥር ስር ባሉ መገናኛ ብዙሃን አልበሙ ሽፋን እንዳያገኝ ከመደረጉም ባለፈ፣ በአዲስ አበባ ‘ሙዚቃውን በማድመጥ አመጽ ትቀሰቅሳላችሁ’ በሚል ውንጀላ 138 ሰዎች ወደ እስር ቤት መጋዛቸው ይታወሳል። ይህም በስልጣን ላይ ያለው የብልፅግና ፓርቲ፣ የአርቲስቱን የህዝብ ተሰሚነት እንደ ከፍተኛ ስጋት እንደሚመለከተው ግልጽ ማሳያ ተደርጎ ተወስዷል።







